የሰራተኞች “የተረጋገጠ ሞት”፦ የናይጄርያ የሰራተኛ ማኅበር አዲሱ የዝቅተኛ ደመወዝ በገዥዎች “ዘላቂ አይደለም” መባሉን ተቸ
የናይጄሪያ የሰራተኛ ኮንግረስ፤ (ኤን.ኤል.ሲ) በቂ ያልሆነ ብሔራዊ ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ፤ በሀገሪቱ የሰው ሃይል ብቻ ሳይሆን፤ በአጠቃላይ ብሔራዊ ኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ አደጋ እንደሚፈጥር አስጠንቅቋል።
ኮንግረሱ፤ ገዥዎቹ ምላሻቸውን በድጋሚ እንዲያጤኑ እና ሀገሪቱን “ከተረጋገጠ ሞት” እንዲከላከሉ አሳስቦ፤ የአብዛኞቹ ክልሎች ኢኮኖሚ በሠራተኞች ደመወዝ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ አፅንኦት ሰጥቷል።
የናይጄሪያ ገዥዎች ፎረም (ኤን.ጂ.ኤፍ) በቅርቡ ባወጣው መግለጫ፤ አዲስ የ60,000 ናይራ ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ (40 ዶላር ገደማ) ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ፤ "ጥቂት ክልሎች ለሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ ለመክፈል መበደር ይኖርባቸዋል" ብሏል።
"ሁሉንም ነገሮች ከግምት ውስጥ በመክተት፤ የናይጄሪያ ገዥዎች ፎረም፤ የ60,000 ናይራ ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ሀሳብ ዘላቂነት እና ተቀባይነት የለውም ብሎ ያምናል። ይህ አብዛኞቹ ክልሎች ሁሉንም የፌዴሬሽን ተቀማጭ ሂሳብ ድልድል ኮሚቴ ምደባዎቻቸውን፤ የልማት ግባቸውን ትተው ደመወዝ ለመክፈል ብቻ ያውላሉ ማለት ነው" ሲል የናይጄሪያ ገዥዎች ፎረም ገልጿል።
ሆኖም የናይጄሪያ የሰራተኛ ኮንግረስ፤ የፌዴሬሽን ተቀማጭ ሂሳብ ድልድል ኮሚቴ ከ700 ቢሊዮን ናይራ (463.6 ሚልየን ዶላር ያህል) ወደ 1.2 ትሪልዮን ናይራ (794.8 ሚልየን ዶላር የሚጠጋ) ማደጉን በመግለጽ፤ ሐሳቡን ውድቅ አድርጓል። ማኅበሩ፤ መንግሥት በሕዝብ ወጪ ሀብት አያከማቸ ነው ሲልም ከሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሰራተኞች “የተረጋገጠ ሞት”፦ የናይጄርያ የሰራተኛ ማኅበር አዲሱ የዝቅተኛ ደመወዝ በገዥዎች “ዘላቂ አይደለም” መባሉን ተቸ
የሰራተኞች “የተረጋገጠ ሞት”፦ የናይጄርያ የሰራተኛ ማኅበር አዲሱ የዝቅተኛ ደመወዝ በገዥዎች “ዘላቂ አይደለም” መባሉን ተቸ
Sputnik አፍሪካ
የሰራተኞች “የተረጋገጠ ሞት”፦ የናይጄርያ የሰራተኛ ማኅበር አዲሱ የዝቅተኛ ደመወዝ በገዥዎች “ዘላቂ አይደለም” መባሉን ተቸ የናይጄሪያ የሰራተኛ ኮንግረስ፤ (ኤን.ኤል.ሲ) በቂ ያልሆነ ብሔራዊ ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ፤ በሀገሪቱ የሰው ሃይል ብቻ... 10.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-10T10:15+0300
2024-06-10T10:15+0300
2024-06-11T11:07+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የሰራተኞች “የተረጋገጠ ሞት”፦ የናይጄርያ የሰራተኛ ማኅበር አዲሱ የዝቅተኛ ደመወዝ በገዥዎች “ዘላቂ አይደለም” መባሉን ተቸ
10:15 10.06.2024 (የተሻሻለ: 11:07 11.06.2024)
ሰብስክራይብ