የምእራቡ ዓለም ለዘመናት አፍሪካ ላይ ለፈፀመው ብዝበዛ ዕዳ መክፈል አለበት፤ ሲሉ የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የምእራቡ ዓለም ለዘመናት አፍሪካ ላይ ለፈፀመው ብዝበዛ ዕዳ መክፈል አለበት፤ ሲሉ የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ ምእራባውያን ሀገራት ዕዳቸውን መክፈል አይፈልጉም አሁን ግን አፍሪካ ላይ ለዓመታት ለፈፀሙት ጉልበተኝነት እና ብዝበዛ፤ ካሳ ስለመክፈል መነጋገር እንደሚያስፈልግ፤ ማሪያ ዛካሮቫ ከ #SPIEF2024 ጎን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አክለውም የቀድሞዎቹ የምዕራባውያን ቅኝ ገዥ ሀገራት "ይህን ማድረግ አይፈልጉም፣ ዕዳቸውን አይከፍሉም፣ የዘረፉትን አይመልሱም፣ ጥፋተኞች ነን ብለው አያስቡም። ነገር ግን ሌላ ጊዜ መጥቷል።" ዓለም ከእያንዳንዱ ሀገር ጋር ለመነጋገር የሚያሳችል ድምጽ በዕድል መልክ ተሰጥቶታል፤ ሲሉ ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል። ብሪክስ፤ በተሳትፏቸው እና አቋማቸውን እንዲገልጹ ዕድል በመስጠት፤ ሀገራት እውነተኛ እኩልነትን እንዲያገኙ ያስችላል፤ ብለዋል ዛካሮቫ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0