ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የማይደርስ ከሆነ መዘዞች እንደሚጠብቁት ኳታር እና ግብፅ ማስፈራራታቸው ተዘገበ
ሁለቱ ሀገራት በአሜሪካ አስተዳደር መመሪያ መሰረት የቡድኑ መሪዎች እስራት፣ የንብረት እገዳ፣ ማዕቀብ እና ከዶሃ ኳታር መሸሸጊያቸው መባረር ሊደርስባቸው እንደሚችል ማስማስፈራራታቸውን፤ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ይሁን እንጂ እነዚህ ጥረቶች ተቃራኒ ውጤት እንዳስከተሉ ሪፖርቱ አመልክቷል፦ ሃማስ ቅድመ ሁኔታዎቹን ያላሟላ ስምምነት ላይ አልስማማም ብሏል።
ባለፈው ሳምንት፤ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እስራኤል ባለ ሶስት ምዕራፍ የስምምነት ሀሳብ ማቅረቧን ገልጸዋል። ስምምነቱ ወደ ዘለቂ የተኩስ አቁም የሚያመራ እና ሁሉም ታጋቾች እንዲፊቱ የሚያስችል ፍኖተ ካርታን ያቀፈ እንደሆነ ተነግሯል።
የመጀመሪያው ምእራፍ የተሟላ የተኩስ አቁም ስምምነት፣ የእስራኤል ወታደሮችን ከሁሉም የጋዛ የህዝብ ማእከላት ማስወጣት እና በሃማስ የተያዙ አንዳንድ ታጋቾችን ማስለቀቅ እንዲሁም እስር ላይ ያሉ ፍልስጤማውያንን ማስፈታት ያካትታል።
ሁለተኛው ምዕራፍ የተቀሩትን ታጋቾች ለማስለቀቅ ጦርነትን ላልተወሰነ ጊዜ ማቆምን ያቀፈ ነው። የስምምነቱ ሶስተኛ ምዕራፍ በጦርነት በወደመችው ጋዛ መልሶ ግንባታ መጀመር ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የማይደርስ ከሆነ መዘዞች እንደሚጠብቁት ኳታር እና ግብፅ ማስፈራራታቸው ተዘገበ
ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የማይደርስ ከሆነ መዘዞች እንደሚጠብቁት ኳታር እና ግብፅ ማስፈራራታቸው ተዘገበ
Sputnik አፍሪካ
ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የማይደርስ ከሆነ መዘዞች እንደሚጠብቁት ኳታር እና ግብፅ ማስፈራራታቸው ተዘገበ ሁለቱ ሀገራት በአሜሪካ አስተዳደር መመሪያ መሰረት የቡድኑ መሪዎች እስራት፣ የንብረት እገዳ፣ ማዕቀብ እና ከዶሃ ኳታር መሸሸጊያቸው መባረር... 09.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-09T12:03+0300
2024-06-09T12:03+0300
2024-06-11T11:07+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የማይደርስ ከሆነ መዘዞች እንደሚጠብቁት ኳታር እና ግብፅ ማስፈራራታቸው ተዘገበ
12:03 09.06.2024 (የተሻሻለ: 11:07 11.06.2024)
ሰብስክራይብ