አሜሪካ ወታደሮቿን ከኒጀር ማስወጣት ጀመረች

ሰብስክራይብ
አሜሪካ ወታደሮቿን ከኒጀር ማስወጣት ጀመረች "የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር እና የኒጀር መከላከያ ሚኒስቴር የአሜሪካ ወታደሮች እና ንብረቶችን ከኒጀር የማስወጣት ሂደት ከመጀመሪያ ዝግጅት ወደ ዝውውር መሸጋገሩን ያስታውቃሉ። ይህ ጉልህ የሆነ ሽግግር የጀመረው የአሜሪካ አየር ኃይል ሲ-17 የካርጎ አውሮፕላን ኒያሚ ከሚገኘው የአየር ማረፊያ 101 ግንቦት 30 ሲነሳ ነው" ብለዋል የሁለቱ ሀገራት መከላከያ ሚኒስቴሮች በጋራ በሰጡት መግለጫ።  በተጨማሪም፤ አንዳንድ የአሜሪካ ወታደሮች ተልእኳቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከኒጀር ወደ መኖሪያ ጣቢያቸው መዘዋወራቸውን፤ መግለጫው አስነብቧል። በተመሳሳይ፤ ጥቂት የአሜሪካ ጦር ሰራዊት አባላት፤ ከኒጀር 101 እና 201 የአየር ማረፊያዎች ወታደሮችን የማስወጣት ሂደት ለማገዝ፤ ወደ አፍሪካዊቷ ሀገር መግባታቸውን ጨምሮ ገልጿል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0