ኢራን የሙስሊም ሀገራት ከእስራኤል ጋር ትብብር እንዲያቆሙ ጠየቀች

ሰብስክራይብ
ኢራን የሙስሊም ሀገራት ከእስራኤል ጋር ትብብር እንዲያቆሙ ጠየቀች የኢራን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ባገሪ ከ ሴኤንኤን ቱርክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "በእኛ አመለካከት የሙስሊም ሀገራት ሊያደርጉ የሚችሉት ውጤታማው ነገር ከእስራኤል አገዛዝ ጋር ያላቸውን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማቆም እንዲሁም ከእስራኤል ጋር የሚደረግ ኢምፖርት እና ኤክስፖርትን ማስቀረት ነው" ብለዋል። አክለውም እስራኤል በቀጠናው ለምትፈጥረው አለመረጋጋት፤ ኢራን ኃይሏን ውጤታማ በሆነ መንገድ በመጠቀም እንደምታስቆም አስታውቀዋል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ በኤክስ የትስስር ገፀፃቸው ይህን አቋም ያስተጋቡ ሲሆን፤ "በጽዮናውያን እቃዎች እና ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ መጣል ቀላል ነገር ግን በጣም ውጤታማ ነው" ብለዋል። አክለውም “በመንግሥታት እና የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ዝምታ" ምክንያት፤ ሀገራት እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፍልስጤምን የመደገፍ ኃላፊነት አለባቸው” ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0