ኢራን የሩስያ እና የምእራቡ ዓለም ወታደራዊ ፍጥጫን እንደ መፍትሄ አልመለከትም አለች
የኢራን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ባገሪ፤ በሩስያ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል የሚታየውን ወታደራዊ ፍጥጫ ለችግር መፍትሄ አድርጋ እንደማትመለከት ገልፀው፤ ለውይይት ጥሪ አቅርበዋል። አክለውም ሀገራቸው "ለሁለቱም ወገኖች የምትመክረው በፖለቲካ አውድ ውይይትን እንዲጠቀሙ ነው" ብለዋል።
በተጨማሪም፤ ኢራን የኒውክሌር መርሃግብሯን የምታከናውነው በአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ መስፈርቶች መሰረት ነው ያሉት ባገሪ፤ ፕሮግራሙ ሙሉ በሙሉ ህጋዊ ነው እንደሆነ ተናግረዋል።
የአይ.ኤ.ኢ.ኤ የገዥዎች ቦርድ የኢራን የኒውክሌር መስፋፋትን የሚያወግዝ ውሳኔ ረቡዕ እለት አጽድቋል።
"ኢራን የኒውክሌር መርሐግብሯን የምታካሂደው በአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ መስፈርቶች፣ ኒውክሌር ክምችት የመቀነስ ስምምነት እና በራሷ ብሄራዊ ፕሮግራሞች መሰረት ነው። የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም እና እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ህጋዊ እና በአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ቁጥጥር ስር ነው” ሲሉ ባገሪ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢራን የሩስያ እና የምእራቡ ዓለም ወታደራዊ ፍጥጫን እንደ መፍትሄ አልመለከትም አለች
ኢራን የሩስያ እና የምእራቡ ዓለም ወታደራዊ ፍጥጫን እንደ መፍትሄ አልመለከትም አለች
Sputnik አፍሪካ
ኢራን የሩስያ እና የምእራቡ ዓለም ወታደራዊ ፍጥጫን እንደ መፍትሄ አልመለከትም አለች የኢራን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ባገሪ፤ በሩስያ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል የሚታየውን ወታደራዊ ፍጥጫ ለችግር መፍትሄ አድርጋ እንደማትመለከት ገልፀው፤... 09.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-09T17:29+0300
2024-06-09T17:29+0300
2024-06-11T11:07+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኢራን የሩስያ እና የምእራቡ ዓለም ወታደራዊ ፍጥጫን እንደ መፍትሄ አልመለከትም አለች
17:29 09.06.2024 (የተሻሻለ: 11:07 11.06.2024)
ሰብስክራይብ