ባይደን፤ ዩናይትድ ስቴትስ ዩክሬንን “አትተውም” አሉ

ሰብስክራይብ
ባይደን፤ ዩናይትድ ስቴትስ ዩክሬንን “አትተውም” አሉ "ዩናይትድ ስቴትስ ከዩክሬን ጋር ጠንክራ ቆማለች፣ ከአጋሮቻችን ጋር ቆመናል፣ ከፈረንሳይም ጋር ቆመናል፣ ደግሜ እለዋለሁ ለዩክሬን ፊታችንን አናዞርም" ሲሉ ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ ከተወያዩ በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተናግረዋል። ሩስያ ካሸነፈች፤ አጠቃላይ አውሮፓ ስጋት ውስጥ ይወድቃል፤ ሲሉም አክለዋል። ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ስዊድንን ጨምሮ ሌሎች የኔቶ አባል ሀገራት፤ ለኪዬቭ በሚያቀርቡት የጦር መሳሪያ ሩስያ ላይ ጥቃት ማድረስ እንዲቻል ፍቃድ ሰጥተዋል። የሩስያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ የኔቶ ሀገራት ዩክሬን የምእራባውያን መሳርያዎችን በመጠቀም የሩስያን ግዛት ለማጥቃት ሲፈቅዱ፤ ከምን ጋር እየተጫወቱ እንደሆነ እንዲያውቁ አስጠንቅቀዋል። የሀገሪቱ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት አደጋ ላይ ከወደቀ፤ ሩስያ በእጇ ያሉ ሁሉንም አማራጮች እንደምትጠቀምም አስምረውበታል። ረቡዕ ከውጭ ጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገው የነበሩት ፑቲን፤ ሩስያ ኔቶን ለማጥቃት ትፈልጋለች የሚለው ሀሳብ ቧልት እንደሆነ ገልፀው፤ "በፍፁም አይገባቸውም ማለት ነው ወይስ አብደዋል?" ሲሉ ጠይቀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0