በ2024 ከአፍሪካ ሀገራት ወደ ሩስያ የሚጓዙ ቱሪስቶች ቁጥር እንደሚያድግ የአስጎብኝዎች ማህበር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
በ2024 ከአፍሪካ ሀገራት ወደ ሩስያ የሚጓዙ ቱሪስቶች ቁጥር እንደሚያድግ የአስጎብኝዎች ማህበር አስታወቀ "ከአፍሪካ ሀገራት ጋር እየጨመረ ከመጣው ትብብር ጋር ተያይዞ ከአፍሪካ ሀገሮች የሚመጡ የንግድ ቱሪስቶች ድርሻ ላይ የተወሰነ ጭማሪ መገመት እንችላለን። የቢዝነስ ቱሪዝም አንቀሳቃሽ ነው፤ ወደ ሩስያ ለመምጣት ዋናው ምክንያት እና መነሻ ነው" ሲሉ የሩስያ የቱሪዝም ኦፕሬተሮች ማኅበር ኃላፊ ማያ ሎሚድዝ ከ #SPIEF2024 ጎን ለስፑትኒክ ገልፃለች። ሆኖም ቻይናውያን በሩስያ የውጭ ቱሪስቶች ድርሻ ውስጥ አሁንም የበላይነት እንደሚኖራቸው አመልክታለች። እንደ ሎሚዝ ገለፃ፤ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ቁጥር ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ እድገት ያሳያል ተብሎ ይጠበቃል። ከቻይና እና አፍሪካ በተጨማሪ፤ የሩስያ ዋና የቱሪስት ፍሰት ምንጮች የመካከለኛው ምስራቅ፣ የደቡብ ምስራቅ እስያ እና የደቡብ እስያ ሀገራት እንደሆኑ ጠቁማለች። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0