የፀረ-ሩስያ ማዕቀብ "ብዙ ሀገሮች የተረዱት እና ራሳቸውን ያራቁበት የምዕራባውያን ስትራቴጂክ ጨዋታ ነው"

ሰብስክራይብ
የፀረ-ሩስያ ማዕቀብ "ብዙ ሀገሮች የተረዱት እና ራሳቸውን ያራቁበት የምዕራባውያን ስትራቴጂክ ጨዋታ ነው" የቡርኪናፋሶ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ማሃማዲ ኩሱቤ ከ #SPIEF2024 ጎን  ለስፑትኒክ እንደተናገሩት "ብዙ የአፍሪካ፣ አውሮፓ ወይም የእስያ ሀገራት ማዕቀቡን አልደገፉትም።" "ምዕራባውያን ዓለምን የመቆጣጠር፤ ሁልጊዜም የበላይ የመሆን ጨዋታቸውን እየተጫወቱ ነው" ሲሉም ተከራክረዋል። "ማዕቀብ ከአሁን በኋላ አይሰራም፤ ምክንያቱም ከትክክለኛ አላማው ባሻገር ፖለቲካዊ ግብ ያለውና ከፍትህ፣ ከህጋዊነት እና ከዓለምአቀፍ ህግ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም" ሲሉም አክለዋል። ምንም እንኳን ገዳቢ እርምጃዎች ቢኖሩም፤ የሩስያ ኢኮኖሚ መቋቋም እንደቻለ እና "ማዕቀቦቹን ከጣሉት ግምት እና ከተጠበቀው በላይ እያደገ እንደሆነ" ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። በሀላፊው እይታ፤ ይህ "ከምዕራባውያን የበላይነት ውጭ መጓዝ የሚፈልጉ ሌሎች ሀገራትን የሚያነሳሳ" ምሳሌ ነው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0