"የሩስያ ነፃ የእህል አቅርቦት ለአፍሪካ የምግብ ዋስትና ወሳኝ ነው" ሲሉ በሩስያ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና ግብርና ድርጅት ግንኙነት ቢሮ ዳይሬክተር ለስፑትኒክ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
"የሩስያ ነፃ የእህል አቅርቦት ለአፍሪካ የምግብ ዋስትና ወሳኝ ነው" ሲሉ በሩስያ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና ግብርና ድርጅት ግንኙነት ቢሮ ዳይሬክተር ለስፑትኒክ ተናገሩ ይህ በተለይ “በከፍተኛ የምግብ እጥረት ችግር” ውስጥ ላሉ ሀገራት ወሳኝ ነው፤ ሲሉ ኦሌግ ኮቢያኮቭ ሴንትፒተርስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የ #SPIEF2024 ጉባኤ ጎን ባደረጉት ቃለ ምልልስ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። "የተላከው እህል ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ህዝቦች አፋጣኝ እና በጣም ወሳኝ የምግብ ድጋፍ ይሆናል። ተጠቃሚዎችንም ዋጋ አያስወጣም። ለተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት እጅግ አስፈላጊ ሚና ይጫወታል፤ ለተራቡ ህዘቦች አስቸኳይ ድጋፍ የሚሆን ነው" ሲሉ አክለዋል። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሩስያ-አፍሪካ ጉባኤ በገቡት ቃል መሠረት፤ ሩስያ በቅርቡ 200,000 ቶን እህል ለቡርኪናፋሶ፣ ዚምባብዌ፣ ማሊ፣ ሶማሊያ፣ ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ኤርትራ አስረክባለች። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0