የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛውን፤ 1 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ዓመታዊ በጀት አፀደቀ
የሚንስትሮች ምክር ቤት፤ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ፤ ለቀጣዩ የ2017 በጀት ዓመት፤ 1 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት አጽድቆ፤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱን አስታውቋል።
የ2017 ዓ.ም የፌደራል መንግስት በጀት፤ የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል በሆነው የ2016-2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ስር የተቀመጡ ግቦችን እና፤ የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል ተድርጎ መዘጋጀቱን ምክር ቤቱ ጠቅሷል።
ምክር ቤቱ በዛሬው እለት ያፀደቀው በጀት፤ "ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልሎች ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ እና ለተጠባባቂ ወጪ እንደሚውል" የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛውን፤ 1 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ዓመታዊ በጀት አፀደቀ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛውን፤ 1 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ዓመታዊ በጀት አፀደቀ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛውን፤ 1 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ዓመታዊ በጀት አፀደቀ የሚንስትሮች ምክር ቤት፤ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ፤ ለቀጣዩ የ2017 በጀት ዓመት፤ 1 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት አጽድቆ፤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱን አስታውቋል።... 07.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-07T20:17+0300
2024-06-07T20:17+0300
2024-06-11T11:07+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий