ሩሲያ እና ዚምባብዌ በጋራ ፍላጎቶቻቸው ዙሪያ ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር ይፈልጋሉ
ቭላድሚር ፑቲን በ2024 የሴንት ፒተርስበርግ አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም #SPIEF2024 ላይ ከዚምባብዌ አቻቸው ኢመርሰን ምናንጋግዋ ጋር እንደሚገናኙና በሁለቱ ሀገራት መካከል የዘለቀውን የረጅም ጊዜ ወዳጅነት በማረጋገጥ፤ አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለመፈተሽ ተዘጋጅተዋል።
እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የቀድሞ ሶቪየት ህብረት ለዚምባብዌ የነፃነት ትግል ጠንካራ ድጋፍ ማድረጓ፤ሁለቱ ሀገራት ላላቸው ጥልቅ እና ዘላቂ ግንኙነት መሰረት ጥሏል።
በ2023 በሩሲያ እና በዚምባብዌ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን 167.8 ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን በ2022 ከነበረው 24.5 ሚሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ እድገት አሳይቷል፣ ሁለቱ ሀገራት በከርሰ ምድር ሀብት ፍለጋ፣ በግብርና ፣ ኢነርጂ እና በትምህርት በጋራ የመሥራት ፍላጎት አላቸው።
የሩስያ አልማዝ፣ ወርቅ እና ፕላቲኒየም ማዕድን አምራች ኩባንያዎች በዚምባብዌ ንቁ ተሳታፊ ሲሆኑ በ2021 በመንግስታዊው ሮሳቶም ስቴት ኮርፖሬሽን እና በዚምባብዌ የኢነርጂ ሚኒስቴር መካከል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙ በኒውክሌር ሃይል ዙሪያ ትብብር ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነትን ያሳያል።
ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋን እ.አ.አ በጥር እና ጥቅምት 2019 እና በሐምሌ 2023 በሩሲያ ያደረጉትን ጉብኝት ጨምሮ መደበኛ የመሪዎች ስብሰባዎች ማድርጋቸው በሀገራቱ መካከል ያለውን ጠንካራግንኙነት ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሩሲያ እና ዚምባብዌ በጋራ ፍላጎቶቻቸው ዙሪያ ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር ይፈልጋሉ
ሩሲያ እና ዚምባብዌ በጋራ ፍላጎቶቻቸው ዙሪያ ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር ይፈልጋሉ
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ እና ዚምባብዌ በጋራ ፍላጎቶቻቸው ዙሪያ ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር ይፈልጋሉ ቭላድሚር ፑቲን በ2024 የሴንት ፒተርስበርግ አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም #SPIEF2024 ላይ ከዚምባብዌ አቻቸው ኢመርሰን ምናንጋግዋ ጋር እንደሚገናኙና በሁለቱ... 06.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-06T14:39+0300
2024-06-06T14:39+0300
2024-06-11T11:07+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሩሲያ እና ዚምባብዌ በጋራ ፍላጎቶቻቸው ዙሪያ ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር ይፈልጋሉ
14:39 06.06.2024 (የተሻሻለ: 11:07 11.06.2024)
ሰብስክራይብ