ቡሩንዲ በአግሪ ቢዝነስ ዘርፍ ከሩሲያ ጋር ተባብሮ ለመስራት ብዙ ትጠብቃለች ሲሉ ሴንት በፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ፎረም ላይ የተሳተፉ አንድ ባለሙያ ለስፑትኒክ ገለፁ

ሰብስክራይብ
ቡሩንዲ በአግሪ ቢዝነስ ዘርፍ ከሩሲያ ጋር ተባብሮ ለመስራት ብዙ ትጠብቃለች ሲሉ ሴንት በፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ፎረም ላይ የተሳተፉ አንድ ባለሙያ ለስፑትኒክ ገለፁ የቡሩንዲ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሬቨርየን ኒዚጊዪማና በዚህ ዘርፍ የሚኖር አጋርነት በጣም ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎችን መኖሩን ዘርዝረዋል። ብሩንዲ የሀገሪቱን"ኢኮኖሚ  እና ልማት ለማሳደግ" ከሩሲያ ቴክኒካል እውቀት ሽግግር እንዲሁም በሀገሪቱ የሚካሄዱ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በገንዘብ መደገፍ አንድትችል ብዙ ትጠብቃላች። በአለም ገበያ ጥራት ያለው ቡና በማቅረብ አንደኛ ደረጃ ላይ የምትገኘዋ አፍሪካዊት ሀገር "ጥራት ቡና መላክ እንድትችል የጥራት ደረጃዎችን በማሟላት ረገድ የሚያጋጥሟትን ተግዳሮቶች ለማለፍ" የሩሲያን እርዳታ ትሻለች። ቡሩንዲ በዘርፉ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ ባለ ሀብቶችን ትፈልጋለች "በተለመደው መልኩ ጥሬ ቡና  ወደ ውጭ መላክ ቀርቶ በአገር ውስጥ  እሴት በመጨመር፤ የስራ እድል መፍጠር ትፈልጋለች"። ይህ  ቡሩንዲ በ2040 መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር ለመሆን፤ በ2060 ደግሞ ከበለፀጉ ሀገራት ተረታ ለመሰለፍር አፍሪካዊቷ ሀገር የያዘቸውን  ራዕይ ለማሳካት ይረዳል  ሲሉ ኒዚጊዪማና ተስፋቸውን ገልጸዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0