ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የምታደርገው ትብብር የጋራ ተጠቃሚነትን ያመጣል ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጉባኤ #SPIEF2024 ላይ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የምታደርገው ትብብር የጋራ ተጠቃሚነትን ያመጣል ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጉባኤ #SPIEF2024 ላይ ተናገሩ "በሩሲያ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው" ሲሉ ማሪያ ዛካሮቫ በጉባኤው ላይ ለተገኙ ጋዜጠኞች ተናግረዋል። "የአፍሪካ አህጉር ባለፉት መቶ ዓመታት በቅኝ ገዢዎች፣ በባሪያ ንግድ እና በዘራፊ መንግስታት ተበዝብዟል።" አፍሪካውያን ከቅኝ ግዛት ለመላቀቅ ባደረጉት ትግል የቀድሞዋ የሶቭየት ህብረት ዋነኛ አጋር እንደነበረች አውስተዋል። "ይህ የሀገራችን ሩሲያ ትልቅ ስኬት ነው፤ብዙ ታላላቅ ስኬቶች አሉን ፤ነገር ግን የሶቪየት ህብረት መንግስት ቅኝ ግዛትን በመቃወም፤ የተሻለ ዓለም እንዲፈጠር  ያበረከተችው አስተዋፅኦ ታሪካዊ  ነው ብዬ እገምታለሁ::" ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0