የግንቦት 29 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የግንቦት 29 ምሽት  ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 ፑቲን ከሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም #SPIEF2024 ጉባኤ ተሳታፊ እንግዶች ጋር፤ ተከታታይ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን ማድረግ ጀምረዋል። ፑቲን ከቦሊቪያው መሪ ጋርም ተወያይተዋል። 🟠 ዩክሬን የዛፖሮዚያ የኒውክሌር ማመንጫን ስለ መምታቷ ማስረጃ አለ፤ ሁሉም የደረሱ ጉዳቶች፣ ሞት እና ውድመት፤ በምርመራው ተመዝግበዋል፣ ሲሉ የዛፖሮዚይ ክልል ገዥ ይቪግኒ ባሊተሰኪ በሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጉባኤ #SPIEF2024 ላይ ተናግረዋል። 🟠 የዩክሬን ጦር ሃይል የሉጋንስክ ህዝቦች ሪፐብሊክን (LPR) እንዲሁም የሉጋንስክ እና የክራስኖዶን ከተሞችን ጨምሮ በምዕራባውያን የረዥም ርቀት የጦር መሳሪያዎች በተደጋጋሚ መምታት መጀመሩን የሉጋንስክ ህዝቦች ሪፐብሊክን ኃላፊ ሊዮኒድ ፓሴችኒክ ተናገረዋል። 🟠 አሜሪካ ለዩክሬን ጦር ሞስኮ እና ክሬ ምሊንን፤ በአሜሪካ ጦር መሳሪያዎች  እንዲመቱ ፈቃድ የመስጠት ፍላጐት እንደሌላት ባይደን ተናግሯል። 🟠 የኔቶ ኃላፊ ስቶልተንበርግ እንዳሉት ከሩሲያ በኩል ምንም አይነት ፈጣን ወታደራዊ ስጋት የለም፤ኔቶም  ወታደሮችን ወደ ዪክሬን የመላክ እቅድ የለውም ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግዋል። 🟠 ስፔስ ኤክስ የፕሮቶታይፕ መንኮራኩር ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳካ ሁኔታ ማረፏን ዘግቧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0