ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት አሥር ወራት ከ2 ሺህ 700 ጊጋ ዋት ሠዓት በላይ ኃይል ማመንጨቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

ሰብስክራይብ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት አሥር ወራት ከ2 ሺህ 700 ጊጋ ዋት ሠዓት በላይ ኃይል ማመንጨቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ ግድቡ የተሻለ ውኃ መያዙና ሁለቱ ተርባይኖች በሙሉ አቅማቸው ኃይል እንዲያመነጩ መደረጉ ፤ባለፉት አሥር ወራት  2 ሺህ 711 ጊጋ ዋት ሠዓት ማመንጨት መቻሉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ ባለፋት አሥር ወራት በአጠቃላይ ከመነጨው የ16 ሺህ 900 ጊጋ ዋት ሠዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 16 በመቶ ድርሻ እንዳለው ተጠቅሷል፡፡ የግድቡ ሁለቱ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን÷ የሚተከሉት ቀሪ 11 ዩኒቶች ኃይል ማምረት ሲጀምሩ እንደሀገር ያለውን የማመንጨት አቅም 83 በመቶ ያሳድገዋል ተብሏል፡፡  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0