የ2024 የሴንት ፒተርስበርግ የኢኮኖሚክ ፎረም አበይት ጉዳዮች
ከ 2005 ጀምሮ የሴንት ፒተርስበርግ የኢኮኖሚክ ፎረም በሩሲያ ፕሬዚዳንት ድጋፍ ሲዘጋጅ ቆይቷል። በዚህ አመት ሰኔ 7 ፤ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ።
የፎረሙ ተቀዳሚ መሪ ሃሳብ "የብዝሃ ዓለም አቀፍ ሥርዓት (Multi Polar )መሠረት መጣል፤ አዳዲስ የእድገት አማራጮችን ማየት" በሚል ተሣታፊዎች ፤ የሀገር ዘላቂ ልማትን ቅድሚያ ከሚሰጣቸው አገራዊ ጉዳዮች ጋር እንዲጣጣም ማድረግ፤ ህብረተሰቡ፣ የንግዱ ማህበረሰብ እና መንግስት እንዴት መተባበር እንደሚችሉ ይወያያሉ።
"ጤናማ ማህበረሰብ፣ ባህላዊ እሴቶች እና ማህበራዊ ልማት፡ ሀገር ቅድሚያ የምትሰጠው ጉዳይ"፣ "ወደ ብዝሃ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት ሽግግር"፣ "የሩሲያ አዲስ የኢኮኖሚ ዑደት ግቦች እና አላማዎች" እና "ቴክኖሎጂ ለአመራር" የሚል አራቱ መሪ ሃሳቦች ናቸው፤ በ2024 የሴንት ፒተርስበርግ የኢኮኖሚክ ፎረም የሚነሱ ጉዳዮች።
በፎረሙ ላይ ከሚሳተፉት የክብር እንግዶች መካከል፡-
የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፌሊክስ ሞሎዋ፦
የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ:-
የቡርኪና ፋሶ የልዑካን ቡድን፣ የኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ሚኒስትር አቡባካር ናካናቦ እና የህዝብ አገልግሎት ሚኒስትር፣ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ካላላ ሚኒስትር ባዚ ባሶልማ:
የሶሪያ የገንዘብ ሚኒስትር ኬናን ያጊ:-
የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሪካርዶ ካቢሪስ ከኩባ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር:-
የቦሊቪያ መሪ ሉዊስ አርሴ ፦
የኦማን ሱልጣኔት ተወካዮች፦
የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒተር ሲጃሪቶ:-
የሲርፕስካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሚሎራድ ዶዲክ;
የቱርክ የኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር አልፓርስላን ባይራክታር:-
የአፍጋኒስታን የታሊባን መንግስት የልዑካን ቡድን ናቸው።
በዚህ ጉባኤ 1,000 የሚሆኑ ሰነዶች ፤የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን ጨምሮ ሊፈረሙ እንደሚችሉ ይጠበቃል። ባለፈው አመት በፎረሙ ከ900 በላይ በድምሩ 42.5 ሚሊዮን ዶላር ውል መፈረሙ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የ2024 የሴንት ፒተርስበርግ የኢኮኖሚክ ፎረም አበይት ጉዳዮች
የ2024 የሴንት ፒተርስበርግ የኢኮኖሚክ ፎረም አበይት ጉዳዮች
Sputnik አፍሪካ
የ2024 የሴንት ፒተርስበርግ የኢኮኖሚክ ፎረም አበይት ጉዳዮች ከ 2005 ጀምሮ የሴንት ፒተርስበርግ የኢኮኖሚክ ፎረም በሩሲያ ፕሬዚዳንት ድጋፍ ሲዘጋጅ ቆይቷል። በዚህ አመት ሰኔ 7 ፤ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር... 04.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-04T19:27+0300
2024-06-04T19:27+0300
2024-06-04T19:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий