የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህወሓት) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድ አዋጅ አፀደቀ፡፡

ሰብስክራይብ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህወሓት) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድ አዋጅ አፀደቀ፡፡ “በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ” የፖለቲካ ፓርቲዎችን “በልዩ ሁኔታ” እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ ነው። ይህ የአዋጅ ማሻሻያ፤ “ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል” በሚል “ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ” የተደረገው ህወሓት በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ መያዙን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ዓርብ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ‘የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ’ እንዲሻሻል ወስኖ ለፓርላማው እንዲቀርብ መወሰኑ ይታወሳል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0