ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው የሚወጡበትን ቀነ ገደብ አስቀመጠች።
የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያ ወታደሮች እ.አ.አ እስከ ታህሳስ 2024 ሶማሊያን ሙሉ ለሙሉ ለቀው እንዲወጡ ቀነ ገደብ መስጠቱን የሶማሊያ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሁሴን ሼክ አሊ ተናግረዋል።
እንዲህ ዓይነቱ ውሳኔ ላይ የተደረሰው፤ ኢትዮጵያ የወደብ እና የባህር ሃይል ጦር ሰፈር ለመገንባት፤ ከሶማሊያ ተገንጥላ ራስ ገዝ ሀገር ከሆነችው ከሶማሊላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) መፈረሟን ተከትሎ ነው።
ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ፣ ባለፈው ጥር ወር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። በስምምነቱ መሰረት ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ለመስጠት፤ ሱማሌላንድ ደግሞ ለኢትዮጵያ የባህር ሃይል ቤዝ እና የንግድ ወደብ እንዲኖራት የሚያስችል ስምምነት ነው ። ይህንን ስምምነት በሞቃዲሾ መንግስት ዘንድ ህገወጥ እና የሶማሌን ሉዓላዊነት የሚጥስ ነው ማለቷ ይታወሳል።
የደህንነት ባለሙያዎች እንደሚሉት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ሶማሊያን ለቅቆ እንዲወጣ መወሰኑ ፤ የፀጥታ ሁኔታው ላይ ክፍተት በመፍጠር ሀገሪቱን የበለጠ እንዳትረጋጋ ያደርጋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው የሚወጡበትን ቀነ ገደብ አስቀመጠች።
ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው የሚወጡበትን ቀነ ገደብ አስቀመጠች።
Sputnik አፍሪካ
ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው የሚወጡበትን ቀነ ገደብ አስቀመጠች። የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያ ወታደሮች እ.አ.አ እስከ ታህሳስ 2024 ሶማሊያን ሙሉ ለሙሉ ለቀው እንዲወጡ ቀነ ገደብ መስጠቱን የሶማሊያ ብሄራዊ ደህንነት... 04.06.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-06-04T16:33+0300
2024-06-04T16:33+0300
2024-06-04T18:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው የሚወጡበትን ቀነ ገደብ አስቀመጠች።
16:33 04.06.2024 (የተሻሻለ: 18:20 04.06.2024)
ሰብስክራይብ