አሜሪካዊው ተዋናይ ጆርጅ ክሎኒ ፋውንዴሽኑ በአውሮፓ ያሉ የሩሲያ ጋዜጠኞችን ለመክሰስ አላሰበም ሲል አስረግጦ ተናገረ።

ሰብስክራይብ
አሜሪካዊው ተዋናይ ጆርጅ ክሎኒ ፋውንዴሽኑ በአውሮፓ ያሉ የሩሲያ ጋዜጠኞችን ለመክሰስ አላሰበም ሲል አስረግጦ ተናገረ። ክሎኒ እንዳለው የፋውንዴሽኑ አንድ ሰራተኛ እራሷን በትክክል አልገለፀችም፤ ድርጅቱ ከጋዜጠኞች ጋር ባይስማማ እንኳን ጋዜጠኞችን አያሳድድም ብሏል። የክሎኒ ፋውንዴሽን አንድ ሠራተኛ ድርጅቱ በዪክሬን እየተሄደ ባለው ግጭት በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ  የሚሰሩ የሩሲያ ጋዜጠኞችን ለማሳደድ ማቀዱ ይታወሳል። የሩሲያ የታችኛው የፓርላማ ምክር ቤት( ዱማ ) ግን በሰጠው ምላሽ አስፈላጊውን መረጃዎች ለአቃቤ ህግ እንደሚልክ እና ክሎኒ ፋውንዴሽን በሩሲያ ውስጥ የማያስፈልግ ድርጅት እንደሆነ ገልፆ ይልካል ፤ብለዋል የምክር ቤቱ ምክትል ሊቀመንበር ቫሲሊ ፒስካሬቭ ። የሕግ አውጭዎቹ በ ክሎኒ ማብራሪያ አልተደነቁም፤ የምክር ቤቱ ምክትል ሊቀመንበር እንደተናገሩት የተዋንያኑ ፋውንዴሽን ፀረ-ሩሲያ እንቅስቃሴዎች በማራመድ የታወቀ ነው ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0