የግንቦት 26 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የግንቦት 26 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ሰርጌ ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን  በጊኒ  ጀምረዋል። 🟠 በቅርቡ በተካሄደው የፓርላማ ምርጫ ገዥው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ከ70 በላይ መቀመጫዎችን ማጣቱን ተከትሎ፤ የደቡብ አፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገሪቱ ጥቅም እንዲሰሩ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጥሪ አቅርበዋል። 🟠 የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሁሴን ሞአሊም ፤ የሶማሊያ መንግስት እ.ኤ.አ. በ2024 መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ከሶማሊያ  እንድታስወጣ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። 🟠 የናሚቢያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጥር 2025 ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ፤ ዝቅተኛ የደመወዝ መነሻ ክፍያን  ለመተግበር ፣የሰራተኛ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እና የስራ እድል ፈጠራ ሚኒስትር ውሳኔውን ማፅደቃቸውን ተናግረዋል። 🟠 ዩክሬን በኬርሰን ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ድንገተኛ ግድያ በተቀነበበረ መልኩ ለመፈጸም  ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ፤በከተማው ውስጥ የሚገኙ የሩስያ ደጋፊ የምስጢር ቡድን ተወካዮች ለሪያ ኖቮስቲ ተናግረዋል ። 🟠 ግብፅ ከሩሲያ ጋር በራሳቸው ገንዘብ ልውውጥ ለማድረግ እየተወያየች ነው ሲሉ የሀገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አስታውቀዋል። 🟠 የገዢው ፓርቲ እጩ ክላውዲያ ሺንባም ከ58.3% እስከ 60.7% ድምጽ በማግኘት የሜክሲኮ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዎችን ማሸነፋቸውተነግሯል። የወቅቱ ፕሬዝደንት፤ ሼይንባን እንኳን ደስ አለዎት! የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። 🟠 ትራምፕ በጁላይ 11 በኒውዮርክ ከሚጠበቀው የፍርድ ቤት ውሳኔ ምንም ይሁን ምን ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት በእጩነት ይቀርባሉ፤ ሲሉ የሪፐብሊካን ብሄራዊ ምርጫ ኮሚቴ ሰብሳቢ ላራ ትራምፕ ለምዕራቡ አለም መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል ። 🟠 ሩሲያ ውስጥ ሰው በሰራሽ አስተውሎ ዘዴ ፤ የተጠቀለሉ ፅሁፎች ሳይገለጡ ለማንበብ እንዲቻል ተደርጓል። የወረቀት ወይም የበርች ቅርፊት ጥቅል ፤​​እንዲሁም  መጻሕፍትን በሲቲ ስካን ማሽን ውስጥ በማስገባት፤ የዲጂታል ቅጂ እንዲሰጥ ተደርጓል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0