የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የምርጫ ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ የህዝቡን ፈቃድ እንደሚቀበሉ ገለፁ

ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የምርጫ ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ የህዝቡን ፈቃድ እንደሚቀበሉ ገለፁ "ወደድንም ጠላንም ህዝባችን ሀሳቡን አሳውቋል" ሲሉ ለተሰበሰበ ህዝብ ተናግረዋል። "በድምፃቸው ዲሞክራሲያችን ጠንካራ እና ፅኑ መሆኑን በግልፅ እና በቀጥታ አሳይተዋል። ምርጫቸውን እና ፍላጎታቸውን ማክበር አለብን።" በመቀጠልም ይህ ምርጫ "የደቡብ አፍሪካ ህዝብ መሪዎቻቸው ፍላጎታቸውን ለማሟላት በጋራ እንዲሰሩ እንደሚጠብቁ" በግልጽ አሳይቷል ሲሉ አክለዋል። ራማፎሳ "የመረጧቸው ፓርቲዎች ለአብዛኛው ህዝብ ጥቅም ሲባል የጋራ ተግባቦት እንዲፈጥሩ እና ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን እንዲሉ ይጠብቃሉ" ብለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0