የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የታገዱ የፖለቲካ ሃይሎች ወደ ነበሩበት የሚመለሱበትን መንገድ ጠረገ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የታገዱ የፖለቲካ ሃይሎች ወደ ነበሩበት የሚመለሱበትን መንገድ ጠረገ ከዚህ በፊት ታግደው የነበሩ ድርጅቶች፤ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሆነው እንደገና እንዲመዘገቡ የሚያስችል ማሻሻያ አዋጅ፤ በኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አርብ ዕለት ተቀባይነት አግኝቷል። የሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማሻሻያውን የሚያጸድቅ ከሆነ፤ እንደ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ያሉ የታገዱ ቡድኖች እንደገና እንዲመዘገቡ በር ይከፍታል። እ.አ.አ 2019 ስራ ላይ የዋለው የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ፤ ከዚህ ቀደም ግጭት ላይ የተሳተፉ ቡድኖች፤ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ማረጋገጫ ቢሰጡም እንኳ፤ ህጋዊነት የሚያገኙበት ድንጋጌ የለውም። እርምጃው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ጌታቸው ረዳ፤ ከሶስት ወራት በፊት የሰጡትን መግለጫ የተከተለ ነው። በሕወሃት የምዝገባ አሰራር ላይ የሚነሱ የህግ ችግሮችን በተቻለ ፍጥነት ለመፍታት ፍለጎት እንዳላቸው ገልፀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0