የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ተጠናቀቀ፦ አጀንዳዎቹ ምን ነበሩ?

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ተጠናቀቀ፦ አጀንዳዎቹ ምን ነበሩ? የኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ፤ የአፍሪካ ልማት ባንክ የገዢዎች ቦርድ አመታዊ ስብሰባን ከሰኞ እስከ አርብ አስተናግዳለች። በዚህ አመት፤ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ፤ የዓለምአቀፍ የገንዘብ አርክቴክቸርን መለወጥ ቅድሚያ ትኩረት የተሰጥው ጉዳይ ነበር። እስከ 2030 የአየር ንብረት የገንዘብ ድጋፍ ጉድለትን ለመሸፈን፤ የአፍሪካ ሀገራት ከግሉ ዘርፍ በዓመት 213 ቢልየን ዶላር ማግኘት እንዳለባቸው ባንኩ አስታውቋል። የባንኩ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል፤ "ኤኤኤ" (AAA) ዕዳ የመክፈል ደረጃውን ለማስጠበቅ ወሳኝ የሆነው ተጠሪ ካፒታል ማሳደግን በተመለከተ፤ ገዥዎቹ ጥልቅ ውይይት እንዲያደርጉ ጠይቋል። ዕዳ የመክፈል ደረጃ በፋይናንስ ገበያ ውስጥ ብድር ለማግኘት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው። የባንክ ቡድኑ አዲሱን የ2024-2033 የ10 ዓመት ስትራቴጂ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ይህም አፍሪካ የተጋረጡባትን አንገብጋቢ ጉዳዮች ለመፍታት እና አህጉሪቱ ወደ ቋሚ የኢኮኖሚ ልማት እና ብልፅግና እንድትመለስ የሚያስችል አጠቃላይ እቅድ ሆኖ የሚያገለግል ነው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0