''ይህ የሙዚቃ ቴክኖሎጂ በእኛ ሀገር ኢንዱሰትሪ ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ መምጣቱ ዕድል ነው። በእርግጥ በኢትዮጵያ የትውውቅ ደረጃ ላይ ነው ያለው ማለት እንችለላለን — ግን በመምጣቱ ብቻ፣ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በመቀላቀሉ ብቻ አዲስ ዓይነት ድምፅ፣ ቅንብር፣ የሙዚቃ መሣሪያ መሥራት ለናፈቃቸው፤ ከዛም ባለፈ የሚፈራ የነበረው አደጋችና አልፊ የነበረው የመሉ ባንድ ዓይነት ስሜት ያላቸውን ሙዚቃዎችን ለመሥማት ዕድልን የፈጠረ ነው '' ሲል በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዙ 'ቀሽቲ' እና 'መኖር' አልበሞች የግጥምና ዜማ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ብርሃኑ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።
ሁለት አንኳር በምንዳስስበት ፕሮግራማችን የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ትውውቅ በኢትዮጵያ ሙዚቃ በተመለከተ በሠው ሠራሽ አስተውህሎት ቴክኖሎጂ እገዛ በራሱ የግጥምና ዜማ ዝግጅት 'ቀሽቲ' እና 'መኖር' የተሰኙ ሁለት አልበሞችን ከሠራው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ብርሃኑ ጋር ቃኝተነዋል። በክፍል ሁለት በአፍሪካ የቢዝነስ አውትሶርሲንግ ካምፓኒዎች ያላቸውን ሚና በጋና የቢዝነስ አውትሶርሲንግ አገልግሎቶች ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ዴቪድ ጋር ዳሰነዋል።
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox