''የኢነርጂ ዋጋ እየተመነጠቀ ነው፣ ተፅዕኖውንም እያስተዋልን ነው፤ የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ከዓለም ፖለቲካ ትይዩ የሆነ ስርዓት መፍጠር ይኖርባቸዋል — የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ድምፅ የሚሆናቸው ያስፈልጋቸዋል፣ በዚህም የስፑትኒክ አፍሪካ ጥረት የሚደነቅ ነው።'' ሲል ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን የሚከታተለው ጋዜጠኛ ቢንያም ካሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።
ሦስት ጉዳዮች በምንዳስስበት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን፣ በክፍል አንድ በኢራን ጦርነት የተዘጋው የሆርሙዝ ሰርጥ በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖን ከጋዜጠኛ ቢንያም ካሴ ጋር ቃኝተነዋል። በክፍል ሁለት ስለአፍሪካ ከተሞች ዕድገት በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የቀድሞ ቴክኒካል አማካሪ ቤካ መገርሳ ጋር ተወያይተናል።
በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ከኃይል አቅርቦት አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ እንደታላቁ የህዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች አማራጭ ምንጭ የመሆናቸውን ሚና በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ጋር ያደረግነው ቆይታም የፕሮግራሙ ሌላኛው አካል ነው።
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበው ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox