The Rising South

የአእምሯዊ ንብረት መብት ተጽዕኖ በአፍሪካ ፋርማሲዩቲካልስ ኢንዱስትሪ ላይ

Sputnik

“አብዛኞቹ የተከናወኑት በምዕራባውያን እና በአውሮፓውያን ነው። ስኮትላንዳዊያን፣ እስያውያን እና አፍሪካውያን ደግሞ በማህበረሰብ ፋይናንስ እና መሰረተ ልማቶች ባላቸው ሰፊ ተደራሽነት ምክንያት ኢንቨስት እያደረጉ ነው። ስለዚህ፣ በርካታ ኢንቨስትመንቶች እንዳሉ እስማማለሁ:: እናም ኢንቨስትመንቱ ሊመለስላቸው ይገባል። ነገር ግን፣ ይህ መሆን ያለበት የፈጠራ ስራዎችን እና ምርምርን በማገድ መሆን የለበትም።” ሲሉ የኪሊች ኤስትሮ ባዮቴክ ኃ.የተ.የግ.ማ መስራችና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በቀዳሚነት የኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ ጋር ስለ አእምሯዊ ንብረት መብት እና መድኃኒት አቅርቦት እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ከመጋቢት 7–9 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተካሄደው የደቡብ አፍሪካ-ኢትዮጵያ የንግድ ፎረም ላይ ተገኝተን የደቡብ አፍሪካ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ውድድር ሚኒስቴር የኤክስፖርትና ማርኬቲንግ ዋና ዳይሬክተር ዛኔሌ ሳኒን እንዲሁም የሉንየዚ ፋርምስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳምኬሊሲዌ ሲቶሌን በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ አነጋግረናቸዋል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox