Sovereignty Sources

የቅኝ ግዛት ባህልን ለመንቀል ቶጎ ያቀረበችው የአፍሪካ አዲስ ዓመት ሀሳብ

Sputnik
''መሠረታዊው ነገር እሪካዊያን ተግባራዊ አንድነት፣ ተምሳሌታዊ አንድነት፣ የፓን አፍሪካኒዝም ወንድማማችነት እንዲሁም ከቅኝ ግዛት ባህል መውጣት ነው በዚህ የቶጎ ጉዳይ ውስጥ እንደ አነሳሽ ሀሳቦች ሆነው የሚታዩት። ደግሞም በተቋም ደረጃ ለምሳሌ ለአፍሪካ ኅብረት ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል - ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የዕዮብዘር ዘውዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።''
በክፍል አንድ የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቶጎ ባህላዊው ቅኝ ግዛትን በመቃወም አፍሪካ የራሷ የዘመን መቁጠሪያ፣ አዲስ ዓመትም ያስፈልጋታል በሚል በይፋ ያቀረበችውን ምክረ ሀሳብን ከተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አውዶች አኳያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የዕዮብዘር ዘውዴ ጋር እንወያያለን፡፡
በክፍል ሁለት ደግሞ በክርስትና እና በእስልምና እምነት ዘንድ ያሉትን አበይት አጽዋማት መነሻ አድርገን ስለመረዳዳትና ሃይማኖቶች እንዴት የማህበራዊ እሴት ማጠናከሪያ እንደሚሆኑ በእስልምና ጥናት ተመራማሪ እንድሪስ ሞሃመድ (ዶ/ር) ቃኝተነዋል፡፡
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox