Drum of Changes

የጸጥታው ም/ቤት በኢራን ላይ ያሳለፈው ውሳኔ እና የሩሲያ '‘መርህ ይከበር'’ ጥሪ

Sputnik
የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ኢራን በባህረ ሰላጤው ሀገራት ላይ የምታካሄደውን ጥቃት በአስችኳይ እንድታቆም ጠይቋል፣ ሩሲያ በበኩሏ ይህ የምክር ቤቱ ውሳኔ “በከፍተኛ ደረጃ ሚዛናዊነት የጎድለው ነው” ስትል አጣጥላዋለች።

“ኢራን የተከፈተባትን ጦርነት በፍትሃዊነት እየተከላከለች መሆኑ እየታወቀ፣ የጸጥታው ምክር ቤት አባላትን እየመረጠ የሚተገብረው ሕግ አሳፋሪ ነው [...] ሩሲያም ተቃውሞዋን ማሰማቷ ለተቀረው ዓለም የሚነግረው መልዕክት ‘የትኛውም አካል ማንም ላይ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ሲል ብቻ ሕጎችን እየመረጠ መተግበር አይችልም’ የሚል ነው” ሲሉ የሕግ ባለሞያ እና የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ትንታኙ አንዷለም በዕውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ወቅታዊ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ያሳለፈውን ዉሳኔና የሩሲያን ተቃውሞ ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን ይዳስሳል። የሕግ ባለሞያ እና የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ትንታኙ አንዷልም በዕውቀቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ሐሳባቸውን ያጋሩናል። ኢፌ አኬንሼዬ (ዶ/ር)፣ ይማሜ ተከተል እና ያው ፍሬድሪክ ዴቪስ ደግሞ በአፍሪካ የማህበረሰብ ትምህርትን በተመለከተ ለምናደርገው ውይይት እንግዶቻችን ናቸው።
ሙሉ መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox