The Rising South

የአፍሪካ ድምፅ በአፍሪካዊያን፦ ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ

Sputnik
“ስፑትኒክን በተመለከተ ፣ እኛ አማራጭን ብቻ ነው የምናቀርበው። የተለየ የዕይታ ነጥብ እያቀረብን ነው፤ እንዲሁም ለደቡባዊው ዓለም አገራት ድምፅ ለመስጠት እየሞከርን ነው። ስለዚህ፣ እኛ ምንም ዓይነት ነገር በማንም ላይ እየጫንን አይደለም። እኛ ያልተነገሩትን ነገሮች እየተናገርን ነው፤ አድማጮቻችን እና አንባቢዎቻችን ደግሞ የራሳቸውን መደምደሚያ እንዲያሳርፉ እንጋብዛለን። ስለዚህ፣ ለደቡባዊው ዓለም አገራት በመገናኛ ብዙኃን ዓለም ውስጥ እንዲህ ዓይነት አማራጭ ማግኘታቸው ትልቅ ዕድል ነው።" ሲሉ የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ አሌክሳንደር ሺፒን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህኛው ልዩ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፍቶ ስርጭት የጀመረበትን 1ኛ ዓመት አስመልክቶ የመጀምሪያው ዓመት የሥራ ሂድት እና አጠቃላይ መልኮችን አስመልክቶ የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ አሌክሳንደር ሺፒን፣ ማኔጂንግ ኤዲተር ፀጋዬ ወንደሰን እንዲሁም አዘጋጅ እና አቅራቢ ከሆነችው ኤደን ተሾመ ጋር ቆይታ አድርገናል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox