Sovereignty Sources

የኔልሰን ማንዴላ ሙዚየም በአዲስ አበባ

Sputnik

''የኔልሰን ማንዴላ ሙዚየም በአዲስ አበባ ሲከፈት ማሟላት ያለባቸውን ነገሮች፣ አንደኛው እሳቸው በነበሩባቸው ጊዜያት ያረፉባቸው ክፍሎች፣ የተጠቀሙባቸው ዕቃዎች፣ የሥልጠና ቦታና የወሰዷቸውን የስልጠና ዓይነቶች ያካተተ ነው — የአሁኑ ትውልድ እንደ አደዋ ካሉ የትናንት የአባቶቻችን ታሪክ ብዙ ተምሮ፣ ይህ መነሻ ሆኖ ለነገው ትውልድ ደግሞ ስንቅ ሆኖ መተላለፍ አለበት።'' ሲሉ ኮማንደር አሳቤ ባይሳ፣ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሎጀስቲክ መምሪያ የንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ኃላፊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በአዲስ አበባ ኮልፌ የቀድሞው የፈጥኖ ደራሽ ግቢ ውስጥ በዘመናዊ መልክ የታደሰውና ስለተገነባው የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ሙዚየም ኮማንደር አሳቤ ባይሳ፣ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሎጀስቲክ መምሪያ በሎጀስቲክ መምሪያ የንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ኃላፊ ሀሳባቸውን ያጋሩናል።
በክፍል ሁለት የግብርና ዘርፍ በገንዘብ መደገፍን መሠረት አድርገን ገበሬዎች ሥራቸውን ለማስፋፋትና ለማጎልበት ከፋይናንስ ተቋማት ብድር ለመውሰድ ስለሚጠየቁት የንብረት መያዣ መሥፈርቶች ጉዳይ በዘርፉ ከዩኒቨርሲቲ መምህርነት እስከ የዓለም የምግብና የግብርና ድርጅት (ፋኦ) ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋሟት የሠሩት ወርቅነህ ወዳጆ አበበ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል።
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox