Sovereignty Sources

ከሩሲያ ለአፍሪካ ወጣቶች የተመቻቸ የትምህርት ዕድል

Sputnik

''ከሩሲያ የነፃ የትምህረት ዕድል ማግኘቴ እንደ አፍሪካዊ ብሎም ኢትዮጵያዊ ሴት እጅግ የሚያኮራኝ ነው። ሁላችንም ለማግኘት የምንመኘው ዕድል ነው። ሩሲያ በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ተማሪዎችን እየመረጠች ዕድል መሥጠቷ፣ የትምህርት ሥርዓት ላይና አዕምሮ ላይ መሥራቷ በጣም ትልቅና ወሳኝ ነገር ነው።'' ስትል በሩሲያ የከፍተኛ ትምህረት ነፃ ዕድል ተጠቃሚዋ ምህረት በፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች።

ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ትምህርት በህብረተሰብ ዘንድ የሚያሳድረውን ማኅበራዊ ተፅዕኖ መሠረት አድርገን የቤተሰብ ደረጃን ለማሻሻል የማኅብረሰብ ልማትንም ለማጎልበት ሴቶችን ማስተማር ስለሚያበረክተው ቁልፍ ሚናን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለረጅም ዓመታት በማስተማር ያሳለፉት ሳምሶን ገብረ ህይወት ጋር ቃኝተነዋል። በክፍል ሁለት ሩሲያ ለአፍሪካዊያን ተማሪዎች ለረጅም አመታት እየፈጠረች ስላለችው የትምህርት እድል የሩሲያ የከፍተኛ ትምህርት ባለዕድል ወጣት ተማሪዎች መካከል ከምህረት በፍቃዱ፣ ናዖል መርጊያ እና ሳሙኤል ብርሃኑ ጋር እንወያያለን።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox