ዛሬ አለምዓቀፉ የሬዲዮ ቀን በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። ስፑትኒክ አፍሪካም በአዲስ አበባ ማህበረሰብ ሬዲዮ 99.4 ኢትዮጵያን ፣ አፍሪካን እና መላው ዓለምን የሚዳስሱ ዝግጅቶችን በአማርኛና በእንግሊዝኛ እያቀረበ ይገኛል።
‘’ [...]ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ በከፈተው ቢሮ ኢትዮጵያን እና አፍሪካን የሚመጥኑ ጠንካራ ይዘቶችን እየሰራ ነው።[...] የስፑትኒክ ጋዜጠኞችን በደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጥናት ምርምርን ሲያቀርቡ አግኝቻቸው ነበር። ይህ የሩስያን ቀናነትና አብሮ የመስራት ፍላጎት የሚያሳይ ነው።” ሲሉ አንጋፋው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬ የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ቀንን መነሻ በማድረግ ፣ ከሬዲዮ ሞስኮ አእስከ ስፑትኒክ በሚል ርእስ እለቱን እዘክራለን። ሬዲዮ ከሌሎች የመገናኛ አዉታሮች የተለዩ የሚያደርጉትን ባህሪያትና ስፑትኒክ አፍሪካ በአዲስ አበባ የቅርንጫፍ ቢሮውን መክፈቱ በመረጃ ፍሰት ላይ የሚኖረውን ሚናም እንዳስሳለን። ለዚህም አንጋፋዎቹን ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች ተፈሪ ዓለሙ እና ጥበቡ በለጠ ጋር በተጨማሪም ስለ ሬዲዮ ሞስኮ ትዝታቸውን ካካፈሉን ከአቶ ማሞ መንገሻ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox