አማራጭ የክፍያ ስርዓት ፣ የፋይናንስ ሉዓላዊነት የእዳ ጫና እፎይታ ለአፍሪካ- አፍሪካ ህብረት ጉባኤ 2026 ''አፍሪካ በፋይናንስ ስርዓቶችና ምህንድስና ረገድ በታሪክ ኢፍትሃዊነትን እየተጋፈጠች ነው። ከምዕራባዊያን ሀገራት ጋር ሲነፃፀሩ የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማቶች እየተበደሩ ያሉት በከፍተኛ መጠን ነው'' ሲሉ የሌሴቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጆኒ ምፖትጁዋና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
48ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ እ.ኤ.አ ከየካቲት 11 እስከ 12 በአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ተደርጓል። የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ እና ሌሎች ጉዳዪች ላይ ተወያይተዋል። በዛሬው ዝግጅታችን በክፍል አንድ የሌሴቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጆኒ ምፖትጁዋና፣ ከኬንያ የካቢኔ ጽ/ቤት ዋይክሊፍ ሙሣሊያ ሙዳቫዲ ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአንጎላ አምባሳደር ፍራንሲስ ዦዜ ዳ ክሩዝ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ጸሃፊ ጂያን ክሪሶስቶም ንጋቢቴሲንዝ (ዶ/ር) ሀሳቦቻቸውን አጋርተውናል። በክፍል ሁለት የምሥራቅ አፍሪካ ምጣኔ ሀብትን መሠረት አድርገን ከኢኮኖሚስቱ ድንቅነህ ገብሬ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox