"በባርነት ዘመን እግሮቻችን ላይ የነበረው ሰንሰለት አሁን እግሮቻችን ላይ የለም፣ ሰንሰለቱ አሁን ያለው አእምሮአችን ላይ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት የባህል ልውውጦች ሲኖሩ፣ በአፍሪካውያን አእምሮ ውስጥ የጥፋት ዘርን በስውር ይዘራሉ። 'ኦ! ምዕራባውያን እንዲህ ያደርጋሉ፤ ያ ደግሞ የላቀ ሥልጣኔ (high class) ነው' እንላለን። ነገር ግን አፍሪካ ራሷ የሰለጠነች ናት። በአፍሪካ ባህል ውስጥ ለሥልጣኔ የሚሆኑ ብዙ ምሳሌዎች አሉ።" ሲል የሚዲያ ባለሙያ እና የድምፅ ተዋናይ የሆነው ኮስሞ ሚለር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡
በዚህ ባለ ሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በመጀመሪያው ክፍል የሚዲያ ባለሙያ እና የድምፅ ተዋናይ ከሆነው ከኮስሞ ሚለር ጋር በመሆን የሥልጣን ተፅዕኖ በዝምታ ነገር ግን በቆራጥነት በሚንጸባረቅበት በቋንቋ፣ በባህል እና በኪነ-ጥበባዊ ወኪልነት ዙሪያ የምንወያይ ሲሆን፤ በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፣ በአዲስ አበባ በተካሄደው 6ኛው የፊንቴክስ የቤት ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ ማስጌጫዎች እና የሕንፃ ማጠናቀቂያ ኤክስፖ ላይ ተገኝተን ስለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ራዕይ በተመለከተ በኤክፖው ላይ ካገኘናቸው ባለሙያዎች ጋር ያደረግነውን ቆይታ አካትተናል፡፡
ሙሉ መረጃው ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox