''ስትራተጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ብሪክስ አሁን ላይ ያቀፋቸው አባል ሀገራት ውስን ቢሆኑም ቁጥራቸው የበለጠ እየጨመረ ሲመጣ የዓለም ፖለቲካ ሚዛንን ለማስጠበቅ አቅሙን ያሳድጋል —ቡድኑ አማራጭ የፋይናንስ ልማትን ይፈጥራል። በዚህ ረገድ አዲሱ የልማት ባንክን ማንሳት ይቻላል'' ሲሉ ታምራት ተስፋዬ፣ የዓለም ወጣቶች ኮንፍረንስ አምባሳደር እንዲሁም በኢትዮጵያ የብሪክስ ተማሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና በሩሲያ የሩድን ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ድግሪ የኢኮሎጂ ተማሪ ለስፑትኒክ አፍራካ ተናግረዋል።
በክፍል አንድ የብሪክስ መሥፋፋት መሠረት አድርገን አዳዲስ አባላት ለዓለም ኃይል ሚዛን መጠበቅ ያላቸውን ሚና ከታምራት ተስፋዬ፣ የዓለም ወጣቶች ኮንፍረንስ አምባሳደር እንዲሁም በኢትዮጵያ የብሪክስ ተማሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና በሩሲያ የሩድን ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ድግሪ የኢኮሎጂ ተማሪ ጋር ቃኝተነዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ 22ኛው የአፍሪካ የፋይን ኮፊ ጉባዔንና ኤግዚቢሽንን መሠረት በማድረግየኢትዮጵያ ቡና ማንነትን በተመለከተ ከምንጩ እስከ ዓለም አቀፍ ሉዓላዊነት ድረስ ያለውን አሻራ የግል ዘርፍ ኢንቨስተሩ ፈለቀ ታደሰ እና ከጂማ ገበሬዎች ሁለገብ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ወንደወሰን በዛብህ ጋር ቆይታን አድርገናል።
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox