Sovereignty Sources

የአፈር ብዝሃ ህይወት፡ ከእግራችን ሥር የሚገኘው ውዱ የተፈጥሮ ኃብት ከምግብ ዋስትና አኳያ ሲቃኝ

Sputnik

''አፈር ውዱ የተፈጥሮ ኃብት ነው። ህይወትም በምድራችን ላይ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው። በዚህም አፈር ሲታመም ሊታከም ይገባል። እንደ ሀገር ለኢትዮጵያ የሚያስፈልገን በየጊዜው ምርምርና ክትትል በማድረግ የአፈር ብዝሃ ህይወት ለምግብ ዋስትና ጥረት የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል'' ሲሉ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ሳይንስ እና ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አለሙ ሌላጎ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ስለአፈር ብዝሃ ህይወት (Soil Biodiversity) እንዲሁም የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጋር በማዛመድ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ሳይንስ እና ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አለሙ ሌላጎ (ዶ/ር) ጋር ቃኝተነዋል። በሁለተኛ ክፍል ስማርት ስልኮች መረጃን የማግኛ ዘዴዎችና ሁኔታዎችን ከመፍጠር አኳያ ያላቸውን ፋይዳዎች እንዲሁም ለተሣሣቱ መረጃዎች አጋላጭነትንም የቴክኖሎጂ፣ የማኅበራዊ ትስስር ሚዲያዎችና የኦላይን ግብይት ባለሙያው አማኑኤል አክሊሉ ጋር እንዳስሳለን።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox