Sovereignty Sources

የአፍሪካ ከተሞች አዳዲስ ገፅታዎች

Sputnik
''የአፍሪካን የወደፊት ራዕይ አሻግረን ስንመለከት፣ ያልተበረዘና ሀገር በቀል እውቀትም የተካተተበት አስተሳሰብ ሊኖረን ይገባል - አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት አዲስ አበባን ጨምሮ በመሠረተ ልማት ግንባታዎችና ራሳቸውን ዲጂቲላይዝድ በማድረግ ሂደት በምርጥነት የሚጠቀሱ ናቸው'' ሲሉ የምህንድስና ባለሙያው ምንተስኖት ታምሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።
ሦስት ጉዳዮችን በምንቃኝበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የአፍሪካ ከተሞች በመሠረተ ልማቶች ዲጂታላይዝ በማድረግ አዳዲስ ገፅታዎች እንዲይዙ የሚደረገውን ጥረት ከምህንድስና ባለሙያው ምንተስኖት ታምሩ ጋር ቃኝተነዋል። በክፍል ሁለት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ህንድ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብርና እንደ ብሪክስ አባልነቷ ያላትን ሚናን በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩመር ሬይ ጋር ዳሰነዋል። በሦስተኛው ክፍል ደግሞ በአፍሪካ ለተሰጥዖዎች የሚሰጥ ዝቅተኛ ዋጋን በማሰወገድ ረገድ አህጉሪቷ እንዴት መትጋት እንዳለባት ናይጄሪያዊው የፊልም ባለሙያና የፓን አፍሪካ አቀንቃኝ ጆንቦስኮል ፖል አሞጎር ሀሳባቸውን አጋርተውናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox