Sovereignty Sources

የአፍሪካ ፀሃይን እንደ አማራጭ የኃይል ምንጭ የመጠቀም ጅምሮች

Sputnik
''ሞሮኮ በፀሃይ ኃይል ዘርፍ በአፍሪካ የምትመራ ሀገር ናት። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በንፅፅር ወደኃላ ካሉ ሀገራት መካከል ነው የምትመደበው። ይሁንና ከሶላር ፓነል ኃይል ለመጨመር አበረታች እቅዶች አሉ። ለምሳሌ የመተሃራ ፓነል ፕሮጀክት አለ፣ ወደ 500 ሜጋ ዋት እንዲያመነጩ የታቀዱ ከ8 በላይ ፕሮጀክቶች አሉ'' ሲሉ ንዋይመድህን አበራ (ዶ/ር)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የኃይል አቅም መጠንን ለማስፋፋት የፀሃይ ኃይልን እንደ አማራጭ ምንጭ መጠቀምን ጉዳይ ከንዋይመድህን አበራ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጋር ቃኝተነዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ለአፍሪካ ውኃ መፍትሔዎችን ለመፍጠር የውኃ መሠረተ ልማትን በገንዘብ መደገፍ(ፋይናንስ) ማድረግ በተመለከተ በመሬትና ውኃ ኃብት ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር ጠና አላምረው (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox