The Rising South

የእንቦጭ አረምን በአረንጓዴ አብዮት ጥቅም ላይ ማዋል በኢትዮጵያ

Sputnik

"በጣና ሐይቅ ያለው የእንቦጭ አረም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስጋት ነው። ምክንያቱም ጣና ሐይቅ በላይኛው ጫፍ ላይ ስለሚገኝ ለግድቡ ተጽእኖ ይኖረዋል።" ሲሉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓሳ ሀብትና የውሃ ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር አያሌው ወንዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ከዶ/ር የህዝቤ ካሳ፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር፣ ከአቶ ደበበ ደፈርሶ፣ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሃይድሮሎጂ እና የተፋሰስ መረጃ መሪ ሥራ አስፈፃሚ እና ከዶ/ር አያሌው ወንዴ፣ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓሳ ሀብትና የውሃ ሳይንስ ተመራማሪ ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ወራሪውን የእንቦጭ አረምን በመዋጋት ረገድ እያደረገች ያለውን ትግል እንመረምራለን።

ዶ/ር የህዝቤ በበኩላቸው ከእንቦጭ አረም ሊገኙ ስለሚችሉ እድሎች "ከእንቦጭ አረም የሚገኙ ባዮፈርቲላይዘሮችን መጠቀም በብዛት የሚገኝ ሲሆን ይህም በሰፊው ጥቅም ላይ ከዋለ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል።" በማለት አክለዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox