''የንፁህ ኢነርጂ ልማት ጉዳዮች ያለ ግል ዘርፉ ተሳትፎ እውን ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚህ የመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት እጅግ ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ — መንግስታት፣ የግል ዘርፎች እንደ ቴክኖሎጂና ልማት ሥራዎች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያውሉ ማነቃቃት ይኖርባቸዋል።'' ሲሉ ቤካ መገርሳ፣ የዘርፉ አማካሪ እና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የቀድሞ ቴክኒካል አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት ጉዳዮች ለውይይት በሚቀርቡበት የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስሰ ፕሮግራማችን፣ በክፍል አንድ የመንግስትና የግል አጋርነት የተቀላጠፈ የንፁህ ኃይል መስፋፋት እንዲፈጠር የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ በተመለከተ ከቤካ መገርሳ፣ የዘርፉ አማካሪ እና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የቀድሞ ቴክኒካል አማካሪ ጋር ቃኝተነዋል። የህግ መሠረት የሌላቸው የውጭ ጣልቃብነቶችን ለማስወገድ አፍሪካ የተቀናጀ ዲፕሎማሲን እንደ መሣሪያ መጠቀም የምትችልበት አግባብን በሚመለከት ኡጋንዳዊው የዓለም አቀፍ ቢዝነስ ባለሙያው ዙብሪ ሉጂያና ምልከታቸውን አጋርተውናል።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox