Sovereignty Sources

የማዕድን ሀብቶችን በአፍሪካ:- የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት የማድረግ እንቅስቃሴ

Sputnik
''ወርቅ በአሁኑ ሰዓት ለምጣኔ ሀብት ዕድገት ቀዳሚ ቦታ የሚሠጠው የማዕድን ዓይነት — አንድ ሀገር ብቻዋን ማደግ አትችልም። ቢያንስ የቴክኖሎጂ ሽግግር መውሰድ ይኖርባታል። በዚህም ከአደጉ ሀገራት ጋር ትብብር መፍጠር የሚጠበቅ ነው። በዚህ ረገድ ከራሺያ ጋር ያለን ግንኙነት ለዘመናት የዘለቀ በመሆኑ በጥሩ መልኩ ነው የሚታየኝ '' ሲሉ በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የጂኦሳይንስ ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር በቀለ አየለ (ዶ/ር) ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል።
ሁለት አንኳር ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የማዕድን ኃብት ዘርፍ በአፍሪካ የምጣኔ ሐብት ዕድገትን ለመፍጠርና ለማፋጠን ስለሚያበረክተው አስተዋጽዖ በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የጂኦሳይንስ ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር በቀለ አየለ (ዶ/ር) ጋር እንወያያለን። ጤናማ ብዝሃ ህይወትን ለመፍጠር አካባቢን እንደ ጠንካራ መሠረት ማድረግ በሚመለከት ደግሞ በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፋኖሴ መኮንን ጋር በክፍል ሁለት እንወያያለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox