Sovereignty Sources

ታላላቅ ሩሲያዊያን ጸሃፊዎች ሲታወሱ፡- ከአሌክሳንደር ፑሽኪን እስከ አንቶን ቼክሆቭ

Sputnik

''የሩሲያዊያን ስነፅሁፎች ጭፍን ጥላቻን አያንፀባርቁም፤ ይልቁን የማኅበረሰቡን ባህል፣ ወግና ታሪክ የሚያንፀባርቁ ናቸው - ከታላላቅ ፀሃፊዎች መካከል የአንቶን ቼክሆቭ ሥራዎች በዓለም ላይ ምርጥ 50 ተውኔቶች መካከል የሚመደቡ ናቸው። በዚህም በሥራዎቹ በትልቅ ደረጃ የሚገለፅ ነው - ሲል'' ከቼክሆቭ ሥራዎች ውስጥ አራቱን ወደ አማርኛ ቋንቋ የተረጎመው ተዋናይና በጥብቅና ሙያ ላይ የሚገኘው ሳምሶን ብሬ ለግሃር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድቷል።

በመጀመሪያው የፕሮግራሙ ክፍል የታላላቅ ራሺያውያን ፀሃፊዎችን ዘመን ተሻጋሪ አሻራን መሠረት በማድረግ ከአሌክሳንደር ፑሽኪን እስከ አንቶን ቼክሆቭ ያሉ ታላላቅ የስነ ፅሁፍ ሰብዕናዎችን ከተርጓሚ፣ ተዋናይና በጥብቅና ሙያ ላይ ከሚገኘው ሳምሶን ብሬ ለግሃር ጋር እንዳስሳለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲሁም በደቡብ - ደቡብ ትብብር ውስጥ ያላትን ሚና በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪው አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ጋር ቃኝተነዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox