The Rising South

ግብርና እንደ የኃይል ምንጭ፦ የአፍሪካ የግብርና ልማት ጥያቄዎች

Sputnik
"የኢትዮጵያ የግብርና ምርት 94 በመቶው በጥሬው ነው ወደ ውጭ የሚላከው። ምንም ዓይነት እሴት አይጨመርበትም። [...] እኔ ማየት የምፈልገው አፍሪካ ራሷን መመገብ ብቻ ሳይሆን ለቀሪው ዓለምም ምግብ ስታቀርብ ነው። አፍሪካ ምግብ ለመግዛት በየዓመቱ ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ እያወጣች መቀጠል የለባትም ስለዚህ ራሷን መመገብ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ የምትተርፍ አፍሪካን፤ በቂ የምግብ ምርት ለውጭ ገበያ የምትልክ አፍሪካን ማየት እፈልጋለሁ።" ሲሉ የግብርና ሳይንቲስት እና ተመራማሪ ፀደቀ አባተ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህ ባለ ሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በክፍል አንድ ከታዋቂው የግብርና ሳይንቲስት እና ተመራማሪ ፀደቀ አባተ (ዶ/ር) ጋር በመሆን አፍሪካ ለምን ልማቷን ለሌላ አካል አሳልፋ መስጠት እንደማትችል፤ እንደ እንሰት ካሉ የሀገር በቀል ሰብሎች አንስቶ እስከ መሬት ፖሊሲ እና ሌሎች ጉዳዮች እንወያያለን። በክፍል ሁለት ደግሞ ኢትዮጵያ እንደ ኦፓል ያሉ ውድ ማዕድናትን በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለማካተት በምታደርገው እንቅስቃሴ ላይ በማተኮር፣ በማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብስራት ከበደ (ዶ/ር) ጋር በመሆን ዳስሰነዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox