Sovereignty Sources

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከየት ወዴት?

Sputnik
35ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ነው። አጋጣሚውን ተጠቅመን ስለኢትዮጵያ እግርኳስ መጠየቅ ወደድናል፡፡

''የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጎል የማይገባበት ሊግ ነበር የሆነ ጊዜ፤ ስታዲየም አካባቢ በነፃነት ተከራይህ መኖር ትችል ነበር ጎል ስለማይገባ፣ ጩኸት ስለማይኖረው። የዚህን ያህል ነፃነት ነበረው'' ሲል ኢትዮጵያዊው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ አያናው ወልደ ሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡

በዚህኛው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የአፍሪካ አህጉር እግር ኳስ ዕድገትና እንቅስቃሴን መሠረት አድርጎ ስለአህጉሪቱ የእግር ኳስ ዕድገት፣ ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ የውጭ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች በኢትዮጵያ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ከፓን አፍሪካ ፉትቦል ፀሐፊው ኦምና ታደለ፣ የእግር ኳስ ጋዜጠኛው አያናው ወልደሚካኤል እና የእግር ኳስ ተንታኙ ልዑል ታደሰ ጋር በጥልቀት ተወያይቷል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox