"ጠንካራ የሆነ አለም አቀፍ የጥቁሮች ድርጅት ሊኖር ይገባል። ያለ እሱ፣ ሁሉም ነገር የቁጣ፣ የተቃውሞ እና የተስፋ መቁረጥ መግለጫ ብቻ ሆኖ ይቀራል። እኛ ጥቁር ህዝቦች ትኩረት ማድረግ ያለብን ገለልተኛ፣ አለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ እና ጠንካራ የሆኑ የጥቁር ተቋማትን በመገንባት ላይ መሆን አለበት።” ሲሉ የግሎባል ብላክ ሴንተር መስራች እና ዋና ፀሐፊ ከአቶ ፀጋዬ ቻማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ ከግሎባል ብላክ ሴንተር መስራች እና ዋና ፀሐፊ ፀጋዬ ቻማ ጋር ስለ ፓን-አፍሪካኒዝም፣ ዓለም አቀፍ የካሳ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች እንወያያለን። በኢትዮጵያ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ባለሙያ ይዘንጋው ይታየው ጋር የኢትዮጵያን አረንጓዴ የሽግግር ጉዞ እና ታዳሽ ኃይልን በተመለከተ ያደረግነው ውይይት ተካትቷል፡፡ እንዲሁም የተስፋ አዲስ ፓረንት ቻይልድሁድ ካንሰር ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ሳራ ኢብራሂም፣ ስለ ሰብአዊ ትብብር፣ በኢትዮጵያ ስላለው የህፃናት ካንሰር ህክምና እና ድርጅታቸው ከሩሲያ ፌዴሬሽን ኤምባሲ ጋር ስላለው የረጅም ጊዜ አጋርነት ያጋሩንን ሀሳብ እናጋራችኋለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple Podcasts – Spotify – Deezer – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox