'' በአፍሪካ ጠንካራ ምጣኔ ሀብት መፍጠር ያስፈልጋል። ለዚህም ኢንዱስትሪውን ማጎልበት፣ ፈጠራዎችን ማስፋፋት በተጨማሪም በእውቀትና ክህሎት መደገፍ ተገቢ ነው - ለአንድ አካል የሚተው ባለመሆኑ የግል ዘርፉንም ያካተተ ትብብርና አጋርነት መፈጠር አለበት። ፖሊሲዎችን መከለስና በሁሉም ዘርፎች ውስጥ ማሻሻያዎችን ማፋጠን ያስፈልጋል'' ሲሉ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ጥናቶች መምህሩ ፍራፊስ ሀይሉ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።
ሁለት አንኳር ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በአፍሪካ ጠንካራ የምጣኔ ሐብት ዕድገትን ለመፍጠር የሠው ኃይልን እንደ መሠረት መጠቀምን በተመለከተ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ጥናቶች መምህሩ ፍራፊስ ሀይሉ (ዶ/ር) ጋር ቃኝተነዋል። የምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ የወደፊት ጂዮፖለቲካ ሁኔታ እና ቀጠናዊ ትስስርን በሚመለከት በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ህግ መምህሩ አበራ ለሚ ጋር ያደረግነው ቆይታ ደግሞ በክፍል ሁለት እንዳስሰዋለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts –Deezer – Spotify – Podcast Addict – Pocket Casts – Afripods – CastBox