Sovereignty Sources

ቬኔዙዌላ፡- የፖለቲካ ጣልቃገብነት እና የሉዓላዊነት ጥሰት ማሳያ

Sputnik

''ቬኔዙዌላ አሁን ላይ የውጭ ጣልቃገብነት ተጠቂ ሀገር ናት። በዚህ በውስጥ አንድነት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ፍትህ መጠየቅ ይኖርባታል - የተፈጠረው ነገር ከቬንዙዌላ ባሻገር ለሌሎች ሉዓላዊ ሀገራት በሙሉ የማንቂያ ደውል ነው '' ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ሄብሶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አጋርተዋል።

ሁለት ዐበይት ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የፖለቲካ ጣልቃገብነትን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ሰሞነኛው የቬኔዝዌላን ጉዳይ መነሻ በማድረግ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ሄብሶ ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ አፍሪካዊያን ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት ከሚልኩት ገንዘብ ባሻገር ያላቸው ሚናን በሚመለከት ከናይጄሪያ ሌበር ኮንግረስ ኮምራድ ኢቼ አሱዚ ምልከታቸውን አጋርተውናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox