The Rising South

የኦንላይን እና ርቀት ትምህርት በኢትዮጵያ፣ ዕድል እና ተግዳሮት

Sputnik
“አንድ ሀገር ማደግ፣ መለወጥ፣ መበልጸግ ካለባት በተማሩ ዜጎቿ ነው የሚወሰነው። አንድ ሀገር ዲሞክራቲክ ለመሆን ካስፈለጋት በተማሩ ዜጎቿን ነው የሚወሰነው። ያልተማረ ህብረተሰብ በፈለከው መስመር ልትነዳው፣ በፈለከው ጊዜ የፈለከውን ነገር ልጭንበት ትችላለህ።” በኦንላይን እና ርቀት ትምህርት ዘርፍ ተመራማሪ ረ/ፕ አደራጀው ተሰማ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ ያለውን በኦንላይን እና ርቀት ትምህርት ዘርፍ ተመራማሪ ከሆኑት ከረ/ፕ አደራጀው ተሰማ (ዶ/ር) በመሆን የዲጂታሉ ዓለም እየተፋጠነ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ወጥ ካልሆነ የኢንተርኔት ተደራሽነት፣ የመሠረተ ልማት ክፍተቶች እና ውስን ከተቋማዊ ዝግጁነት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ውስብስብ እውነታ ተደቅኖባታል።

በኢትዮጵያ የኦንላይን እና ርቀት ትምህርት ዘርፍ በአሁኑ ወቅት ውጤታማ የሆኑትን ነገሮች፣ ሥርዓቱ ክፍተት ያለባቸውን ነጥቦች እና የዲጂታል ትምህርት ጥቂት ዕድሉ ያላቸውን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ተማሪዎች እንዲያገለግል ምን መለወጥ እንዳለበት ውይይት አድርገናል። በተጨማሪም የኦንላይን እና ርቀት ትምህርት ዕውቀትን ለሁሉም ለማዳረስ የሚረዳ መሣሪያ ነው ወይስ በከተማ እና በገጠር ማህበረሰቦች መካከል ያለውን ልዩነት የሚያሰፋ? የሚለውን እና ተያያዥ ጉዳዮችን እንዳስሳለን፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ :

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox