Sovereignty Sources

ብሔራዊ የልማት ዕቅድ ከዓለም አቀፍ የባንክ አሰራሮች አንጻር ዕድሎችና ተግዳሮቶች

Sputnik
''ሀገር ሊያድግና ሊለወጥ የሚችለው በውስጥ አቅም ነው፤ በብድርና ድጋፍ ብቻ የተለወጠ ሀገር የለም። ስለዚህ የውስጥ አቅምን በሚገባ አውጥቶ መጠቀም ያስፈልጋል '' ሲሉ በባንክ ዘርፍ በተለይም በማርኬቲንግና ብራንዲንግ የረጅም ዓመታት ልምድ ያካበቱት አሰቻለሁ ታምሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በብሔራዊ ልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ከዓለም አቀፍ የባንኪንግ ልምዶች እንዴት ማዛመድ ይቻላል የሚለውን ጉዳይ በባንኪንግ ዘርፍ በተለይም በማርኬቲንግና ብራንዲንግ የረጅም ዓመታት ልምድ ያካበቱት አሰቻለሁ ታምሩ ጋር ቃኝተናቸዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአዝዕርቶችን አቅም በማሳደግ፣ ምርታማነትን በመጨመር እና የስርዓተ ምግብ ጥራቶችን ማሳደግ በተመለከተ ከአግሮኖሚስቱና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የደጋ ፍራፍሬና አትክልት ምርምር ማዕከል ዳይሬከተር ዘነበ መኮንን(ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox